=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
:☀:በአእምሯችን የሚንሸራሸሩ ሃሳቦች በሂወታችን ለሚከሰቱ ነገሮች ሁሉ ምክኒያት ናቸው። ሃሳባችን በባህሪያችን እና በዝንባሌያችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ሲሆን ተግባራችነን ይቆጣጠራል። ስለምናስበው ነገር ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
ሃሳቦቻችን ልክ እንደ ቪዲዮ ካሴት በአእምሯችን የምንጫወታቸው ናቸው። የምንጫወተው ነገር የምናየው ነገር ሲሆን የምናስበው ነገር ደግሞ የምንኖርበት ሁኔታ ነው።
በህይወታችን ለውጥ ለምጣት አሮጌውን የቪድዮ ካሴት አውጥተን በአዲስ መተካት አስፈላጊ ነው። እፅዋቶች ጠንካራና ጤናማ ሁነው እንዲያድጉ አዝዕርቶችን ውሃ እናጠጣቸዋለን፤ ማዳበሪያ እንነሰንስላቸዋለን አይደል? ሃሳባችንም ልክ እንደ አዝዕርት ናቸው። በአስተሳሰባችን ለውጥ ለማምጣት፤ አስተሳሰባችነን ፈር ለማስያዝ አእምሯችነን በእውቀት ፣ በጥበብ ፣ በመልካም ራዕይ ፣ በመልካም ስራዎች ልናንፅ ይገባል።:☀:
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|